ምላሳችንን ለመፈወስ ጊዜው አሁን ይሆን?
- Betel Christ Church
- Mar 12, 2021
- 4 min read
ምላሳችንን ለመፈወስ ጊዜው አሁን ይሆን?
እስቲ የሆድ የሆዳችንን ከመነጋገራችን በፊት ፈጣሪ የሰው ልጅን ጭንቅላት እንዴት ዲዛይን እንዳደረገው አንዳንድ ጠቃሚ ነጥቦችን ላንሳ።
እግዚአብሄር በሰው ጭንቅላት ላይ ሰባት ቀዳዳዎችን ፈጥርዋል። ሰባት፣ ሰባት በመጠሃፍ ቅዱስ ውስጥ በተደጋጋሚ ሙሉነትን ለማመላከት የሚጠቀስ ቁጥር ነው፣ 2 አይኖች፣ ሁልት ጆሮዎች፣ ህሉት የአፍንጫ ቀዳዳዎች፣ እንዲሁም አንድ አፍ።
ምነው ከአንድ በላይ አፍ በኖረን ብላችሁ ተመኝታችሁ ታውቃላልችሁ? ወይም ቢኖር ብላችሁ አስባችሁት ታውቃላችሁ?
በኔ በኩል ሰለሁልት አፍ መፈጠር ሲያነሳ የሰማሁት ሰው እንኩዋን የለም። ብዙዎቻችን አንዱን አፋችንን እንኩዋን በአግባቡ ለመጠቀም እለት በእለት እንሞክራለን።
ይሀኛው አንዱ የተከፈተው የጭንቅላት ክፍል ከሌሎቹ ጥምር ስድስቱ ቀዳዳዎች ይልቅ በተለየ ሁኔታ ውዝግብ ሲያስነሳብን ይስተዋላል።
በመጠሃፍ ቅዱስ ሰልዚሁ ሰለአፍና ከአፍ ጋር የተገናኙትን ከንፈር፣ ምላስ፣ድምጥ፣ ቃላትና ሰለመሳሰሉት የተነገሩ ብዙ የሚያስገርሙ መለእክቶች ይገኛሉ። ወደ 70 የሚሆኑ ጥቅሶች አሉ። ምላሳችንና አፋችን በቀጥታ ከመላው የሰውነታችን ጤና ጋር እንደሚገናኝ መጥሃፍ ቅዱስ ይናገራል።
በዛሬው መለክቴ ሰለአፍና ምላስ ወሳኝነት የተጣፉትን የመጥሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች ካሉት እውነታዎች ጋር ላካፍላችሁ ወድጄአለሁ።
የመጀመርያው መዝሙረ ዳዊት መራፍ 34 ከቁጥር 11/13 እንዲህ ይላል
ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
12 ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?
13 አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።
እንደእግዚአብሄር ልጅነታችን መጥሃፍ ቅዱስ የእግዚአብሄር ፍርሃት እንዲኖረን ያስተመረናል።
ትእግዚአግቤርን በመፍራት ውስጥ ታላቅ መባረክ፣ ፍሪያማነትና መተማመኛ ኢንሹራንስ እንዳለ ያልተጠቀሰበት ይመጠሃፍ ቅድዱስ ክፍል የለም። መጥሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄርን ሰለመፍራት ታላቅነት ሲያሰርዳ መለኪያ መስፈርት በሌለው ሁኔታ ነው፣ ህይወትና መልካም ቀናቶች እግዚአብሄርን ከምፈራት ጋር እጅና ጉዋንት እንደሆኑ ነው የሚያስረዳው። የህይወት ሙሉነትና ፈሪሃ እግዚአብሄርም እንዲሁ ልዩ ት ሥ ስር አላቸው። እውነትኛ አኑዋኑዋር አለን ብለን ማውራት የምንችለው ባለን እግዚአብሄርን የመፍራት መጠን ነው።
እግዜአብሄርን መፍራት የሚጀምረው ከምንደነው ?
ግልጥ የመስለኛል ለብዙዎቻችሁ።
አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ። የሚል ቃል ነው በመጥሃፍ ቅዱስ የጥፎ የሚገኘው። በሌላ አገላለጥ እግዚአብሄርን መፍራታችን የሚገለጥበት የመጀመርያው በአፋችንና በምላሳችን ነው። አፋችንን ከክፋት ከከለከልን፣ ምላሳችንንም ከውሸት ከጠበቅን ሙሉ በሙሉ እግዚአብሄርን ወደ መፍራት ጎዳና ነው የምንራመደው።
ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት እግዚአብሄርን ከምፈራት ጋር የህይወትና ምልካም ዘመናት ት ሥ ስር አላቸው። አንደበትን በተገባው መልኩ በመጠቀምና ምላሳችንንና ከንፈራችንን በመቆጣጠር እግዚአብሄርን መፍራት ከህይወትና ከመልካም ቀናቶች ጋር የተቆራኙ ናቸው።
ምላሳችንንና አፋችንን የማንቆጣጠር ከሆነ ግ ን የእውነት ደስተኛ ሆነን መኖር አንችልም።
መጥሃፈ ምሳሌ መራፍ 13 ከቁጥር 3 ላይ አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋትን ያገኘዋል። ይላል።
እዚህ ላይ ነው እንግዲህ መጀመርያ የሰው ለጅ ድካም የሚገለጠው ፣ጠላት መግቢያ ቀዳዳ የሚያገኘው። ነፍሳችንን ማዳን ከፈለግ ን ከንፈራችንንን መጠበቅ አለብን። በዘፈቀደ የምናወራ ከሆነ ነገር ማበላሸታችን አይቀርም።
አማራጮቹ ግልጥ ናቸው!
አፋችንን የምንቆጣጠር ከሆነ ከሚጠፋው ጥፋት እንተርፋለን,ምላሳችን ግ ን ዝምብሎ የሚያመልጠው ከሆነና ቃላቶቻችንን ላይ የማዘዝ ስልጣን ከሌለን ይፈረድብናል። ምንም የሚያከራከር ክፍተት የለም እዚህ ላይ።
እንዚህ ሃሳቦች በመጠሃፈ ምሳሌ ላይ ተጥፈው ይገኛሉ። ለምሳሌ መጠሃፈ ምሳሌ 21፣23 ላይ
አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል። ይላል።
መጥሃፈ ምሳሌ 12፣18 ላይ ደግሞ፣
እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ፤ የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው።
ምርጫው የነጭና የጥቁርን ያህል የማያምታታ ግልጥ ያለ ነው። አፍንና ምላስን በመጠበቅ ነፍስንና መንፈሰን ማዳን አሊያ ባለመጠብቅ የሚመጣውን መአት መቀበል ነው።
መአት የሚለው ጠንከር ያለ ቃል ነው፣ ይሁንና በመጥሃፍ ቅዱስ ሆን ተብሎ በተደጋጋሚ ተጠቅስዋል። ከንፈራችንንና ምላሳችንን መጠበቅ ካልቻልን በመጨረሻ ጥፋት ነው የሚከሰተው። ስለ ምላስ አጠቃቀም 2 መራፎች አሉ በመጥሃፈ ምሳሌ።
ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል። መጥሃፈ ምሳሌ 15፣4
በመሆኑም ደስተኛና ጤነኛ ይህወት መምራት እንድንችል ምላሳችንን ከመጥፎ ንግግር መጠበቅ ይኖርብናል።
መጠሃፈ ምሳሌ 18፣21 ደግሞ
ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።
አማራጩ ግልጥ ነው ህይወት ወይም ህይወት አልባ መሆን። ሁልቱም በምላስ ላይ ሀይል አላቸው።
ምላሳችንን በአግባቡ ከተጠቀምንበት የህይወት ዛፍ ካልተጠቀምንበት ደግሞ ውጤቱ ሞት ነው የሚሆነው።በየትኛውም መንገድ ምላሳችንን ብንጠቀመበት በርግጠኝነት ፍሬውን እንበአለን።
እያንዳንዳችን የምንመገበው የምላሳችንን ፍሬ ነው። ፍሬው ጣፋጭ ከሆነ ጣፋጭ ፍሬ እንበላላእን፣ ፍሬው መራር ከሆነም መራር ፍሬውን መመገባችን ግድ ይላለ፣ ህይወትና ሞት ያለው በምላሳችን ላይ ነው።
የያእቆብ መለክት 3፣2/3 ላይ
ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።
እነሆ፥ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናገባለን፥ ሥጋቸውንም ሁሉ እንመራለን።
እነሆ፥ መርከቦች ደግሞ ይህን ያህል ታላቅ ቢሆኑ በዐውሎ ነፋስም ቢነዱ፥ የመሪ ፈቃድ ወደሚወደው ስፍራ እጅግ ታናሽ በሆነ መቅዘፊያ ይመራሉ።
እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ ብልት ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ፥ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል።
6 አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።
የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፥ ደግሞ ተገርቶአል፤
8 ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው።
9 በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤
10 ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።
11 ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውኃ ያመነጫልን?
12 ወንድሞቼ ሆይ፥ በለስ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውኃም ጣፋጭ ውኃ አይወጣም።
የሚል መለክት ተጥፎ ይገኛል፣ በያእቆብ መለክት ።
በሚቀጥለው ክፍል በዘፈቀደ መናገር እንዴት ይህወት ላይ ተጠኖ እንደሚያመጣ እናያለን ፣
እስቲ አሁን እንጠልይ!
እግዚአብሄር አምላካችን ሆይ፣ በቃልህ በተናገርክ ጊዜ ዩንቨርስ ዲዛይን ተደረግ። ቃልህ ሃያልና ጠንካራ ነው። እኛንም በአምሳልህ የፈጠርከንን ደግሞ በምንናገረው ቃል ሃይል አለ ብልህ ነገርከን።
ስለምንናገረው ንገር የምንጠነቀቅና እውነትን የምንናገር እንድንሆን እርዳን!
ለመስማት የፈጠንን፣ ለመናገርና ለቁጣ የዘገየን እንድንሆን እርዳን።
በቃልህ መርገምተም መባረክም የሚመንጨው ከአፍ ነው ብልሀናል።
አንተን ባመሰሀንበትና በባረክነበት ምላሳችን በአነት አምላክ የተሰራውን ሰው ደግሞ እንረግማለን፣
ጊታ እየሱስ ክርስቶስ ስለዚህ አብዛኛውን ጊዜ መርዝ ሰለሚረጨው ምላሳችን ይቅር በለን ።
\ልባችንን ቀይረው ጊታ ሆይ፣ ከልባችን በመነጨው በአፋችን እንናገራለንና!
ምህረት አድርግለን ጌታ ሆይ ህይውትም ሞትም በምላሳችኡ ጉለብት ላይ ነው ብለሃልና።
በምላሳችን፣ ስህተት ነቃሾች ፣ፈራጆች፣ሃሜተኞች፣ ክፉ፣ ስለሆንን ይቅር በለን።
እባክህ አምላካችን ሆይ፣ በዙርያችን ላሉ ሰዎች ህይወትና ተስፋ እናገር ዘንድ እርዳን።
መልካም ቃላቶችን በመናገር በፍቅር እንራመድ ዘንድ፣ መንፈስ ቅዱስንም እንዳናሳዝን እርዳን።
የሚፈውሱ ቃላቶችን እንናገር ዘንድ ፣ምላሳችንን በጥበብ እንጠቀመበት ዘንድ ጠጋውን ስጠን። መልካም ምላስ የህይወት ዛፍ ነውና!
የሌሎችንም ሰዎች መንፈስ መስበር አንፈልግም፣በአንደበታችን ላይ ጠባቂ እንድታዝልንና ከችግር እንደታወጣን እንለምንሃልሁ!
መቼ ማውራት እንዳለብን፣ መቼ ዝም ማለት እንዳለን፣ መቼ መጠለይ እንዳለብን እንረዳ ዘንድ አስተምረን።
ስንናገርም እውነትን በፍቅር መናገር እንድንችል እርዳን። ምላሳችንንም ባለመቆጣጠር የተነሳ በስራችን ግድፈት እንዳይፈጠር ሌሎችንም እንዳናሰናክል ጠብቀኝ።
ከንፈሮቻችንን ክፋት ከመናገር በመጠበቅ በመልካም አንደበት ማደግ እንድችል እርዳን።
ስለሰጠህን ጠጋ አናመሰግናለን።
አሜን!
Comments